የጌታችንና የመድኃኒታችንን ልደት ክብረ በዓል ታህሳስ 26 2018 ዓ.ም.
January 04, 2026 | news
የጌታችንና የመድኃኒታችንን ልደት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ ልጆች የክርስቶስን ፍቅር ትህትና እንዲርዱ በተማሪዎች ድራማ፣ በወንጌላዊ ግሩም የቃል ጊዜ፣ በወላጅ ምስክርነት፣በእስጥፋኖስ ዝማሬ ታላቅ ፍቅሩን አወድሰናል በመጨረሻም ማእድን በህብረት ቆርሰናል፡፡እንዲሁም በተጨማሪ የተሰጠንን ልዩ ስጦታ ኢየሱስ ክርስቶስን በማሰብ እኛም ደግሞ ለእርሱ የምንሰጠው ውድ ስጦታ አምልኳችን ነውና ከዝማሬና ከምስጋና በተጨማሪ ለልጆቻችን በመስጠት እንድናመልከው ወደናል። እንደሚታወቀው በቤተክርስትያናችን እርዳታ የሚያሻቸው ልጆች ከሌሎች ሁሉ ነገር ከሞላላቸው ልጆች ጋር አብረው ይዘምራሉ፥ የሰንበት ትምህርት ይማራሉ። እነሱን በማሰብ ባስተላለፍነዉ የአልባሳት ድጋፍ ማስታወቂያ ከ150 በላይ ለሚሆኑ ልጆች የሚሆን የተለያዩ ልብሶች ጫማዎችን እና የአልባሳት እገዛና ድጋፍ ለሚያሻቸው የሰንበት ትምህርት ተማሪዎች ላደረጋችሁላቸው አቅራቦት፣ ፍቅራችሁንም ደግሞ በተግባር ስለገለፃችሁላቸው የሰንበት ትምህርት አገልግሎት ክፍል ልባዊ ምስጋና ያቀርባል። በተለይም ይህ መልካም ድርጊት እንዲሳካ በውጪና በሀገር ውስጥ ያሉትን የቤተክርስቲያን አባላት ያስተባበረችውን የቤተክርስቲያናችንን ዘማሪት እየሩሳሌም ዮሐንስ (ጄሪ)ን እግዚአብሔር ዘመኗንና አገልግሎቷን ይባርክ እንላለን። በዕለቱ በነበረን የ ሰንበት ትምህርት አገልግሎት ባሳለፍነዉ የክርስቶስ የልደት በዐል ላይ በተለያዩ ነገሮች የድጋፍ አስተዋፅዖ ላደረጉልን አካላት የምስጋና የምስክር ሰርተፍኬት አበርክተናል። 1. ዘማሪት እየሩሳሌም ዩሀንስ 2. ወ/ሮ ጽዮን ተስፋዮሐንስ እና ልጇ ክርስቲና ልጅ 3. ወ/ሮ ረድኤት ኪዳኔ 4. ክርስቲና ዳናኤል 5. የአደይ አበባ ባለቤት በመቀጠል ከጎናችን ለነበራቹ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና አባላት በሙሉ እግዚአብሄር ዘመናችሁን ይባርክ። ድጋፉም ይቀጥላል “ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።”ምሳሌ 19:17