የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ሉትራን ቤተክርስቲያን

አዲስ አበባ አጥቢያ - የሰንበት ት/ት አገልግሎት ክፍል

 

የክረምት ካምፕ ነሃሴ 2017 ዓ.ም.

September 06, 2025 | news

የክረምት ካምፕ ነሃሴ 2017 ዓ.ም. እንደሚታወቀው ክረምት ላይ ሰንበት ትምህርት ስለማይሰጥ ለታዳጊ ተማሪዎቻችንን ልዩ ትኩረትን በመስጠት እና ህይወት ከመቅረጽ ኣኳያ በሁለት የእድሜ ክልሎች ተከፍለው።

1) 12-13 እድሜ ክልል ላይ ላሉ ልጆች በመጽሃፍ ቅዱስ ትምህርት ፣ በአንድነትጊዜ፣ በመንፈሳዊ ፊልሞች ፣በተለያዩ ስልጠናዎች፣ውይይቶች፣ ጨዋታዎች እንዲሁም የተለያዪ ተግባራት ተካሂዷል። በተማሪዎቻችንም ላይ ያየናቸው ለውጦች ክርስቶስን ማእከል ያደረገ ህይወት ምንነትን ፣መንፈሳዊነትን ፣ከአስተማሪዎቻችው ጋራ ልዩ መቀራረብን ፣ የህይወት ለውጥን ፣ግልጽነትን፣ በእኛም ላይ ያላቸው ታማኝነት እና የመሳሰሉትን ማየትና ማሳደግ ችለናል።
2) ከ14+ እድሜ ክልል ላይ ላሉ ልጆች ከቤተ ክርስቲያን ወጣት ኮሚቴዎች ጋራ በመተባበር ለልጆቻችን በመጽሃፍ ቅዱስ ትምህርት ፣ ስለባህሪ ፣ የአቻነት ግፊት፣ የተቃራኒ ጻታ ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን ወስደዋል እንዲሁም professional አሰልጣኝ ከውጪ በመጋበዝ የተለያዩ ተግዳሮቶቻቸው ላይ ያተኮሩ ግንዛቤ ተሰጥቷቸዋል በዚህ እድሜ ክልል ላይ ያሉ ታዳጊዎችም በተመሳሳይ በህይወታቸው ብዙ ለውጦችንም መመልከት ችለናል።