የሰንበት ትምህርት የዓመቱ የመዝጊያ እና ሽልማት ሐምሌ 27 2017 ዓ.ም.
August 03, 2025 | news
ለተማሪዎቻችን ማነቃቂያ ቀን ነበር በእለቱም የአምልኮ ፕሮግራም ተካሄዷል በሰንበት ትምህርት ተማሪዎችም የጥቅስ እና የዝማሬ አገልግሎት ቀርቧል ልጆቻችንን በይበልጥ በወላጆቻቸው እና በቤተ ክርስቲያን አካላት ፊት በመሸለማቸው የተበረታቱ ሲሆን በአመቱ የተከናወኑ ተግባራት እና በአገልግሎቱ የተገኘውን ውጤት ለምዕመናን በማሰማት ጌታን አክበረናል አንዲሁም በነሃሴ 1 በወንድም ፋሲል ጸጋዬ ድጋፍ ከ1 እስከ 3 ለወጡ ተማሪዎች በሙሉ ማበረታቻ ይሆን ዘንድ በደብረዘይት ሄደው በኦርክ ሚኒስትሪ ውስጥ ልዩ ፕሮግራም ተዘጋጀቶ ተሸልመው እንዲሁም ኩሪፍቱ ቃለህይወት ተዝናንተዋል። እግዚአብሔር በእጅጉ ረድቶናል ስሙ ይባረክ።